ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ - Connect for Culture Africa - Ethiopia cover art

ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ - Connect for Culture Africa - Ethiopia

ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ - Connect for Culture Africa - Ethiopia

By: Connect for Culture Africa
Listen for free

About this listen

የሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት በባህል እንዲሁም በኢትዮጵያ በሚገኙ የባህላዊ እና የፈጠራ ኢንዱስትሪ (CCIs) ላይ ያተኮረ ተከታታይ ክፍሎች ያሉት ጥልቅ ውይይት የሚካሄድበት ፖድካስት ነው፡፡ ሃሳብን በሚኮረኩቱ የተለያዩ ክፍሎች ባለሞያዎችን እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ከህዝብ/መንግስት ድጋፍ አንስቶ እስከ ስራ ፈጠራ፣ ሰላም ግንባታና እና ዲሞክራሲ ባህል በኅብረተሰብ ውስጥ ያለውን ሚና ይዳስሳል፡፡ በተሾመ ወንድሙ የሚዘጋጀው ይህ ፖድካስት ለቅስቀሳ እንዲሁም ወጣቶችን ለማብቃት መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ሁሉም ክፍሎች በአማርኛ የሚቀርቡ ሲሆን የእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ይኖራቸዋል፡፡ የበለጠ ለማወቅ የሚከተለውን ድረ-ገጽ ይጎብኙ https://cfcafrica.org The CfCA Ethiopia Podcast is a series of powerful conversations around culture and the cultural and creative industries (CCIs) in Ethiopia. Through thought-provoking episodes, we engage with experts and stakeholders to explore the value of culture in society—from public funding and job creation to peacebuilding and democracy. Hosted by Teshome Wondimu, the podcast also serves as a tool for advocacy and youth empowerment. All episodes are in Amharic with English subtitles. Tune in and explore more at https://cfcafrica.org2025 Art Entertainment & Performing Arts
Episodes
  • Writing Our Truths: The State of Literature in Ethiopia - CfCA - Ethiopia #7
    Aug 29 2025

    የሀገር ገፆች፡ የስነ-ጽሁፍ ሁኔታ በኢትዮጵያ

    ክፍል 7 - ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት

    ደራሲ የዝና ወርቁ እና ተሾመ ወንድሙ በጋራ በመሆን በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችንና እድሎችን ይዳስሳሉ፡፡ የንባብ ልምድ ከማዳበር እስከ ፖሊሲ አስተዋጽኦ፣የህትመት ችግሮች፣ የቋንቋ ብዝኃነት እና ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን በመግለጽ ረገድ የዘርፉ መፃኢ እጣ ፈንታ በዚህ ውይይት ይነሳሉ፡፡

    የሚካተቱ ርዕሶች ዝርዝር

    ጸሀፊዎች በኅብረተሰብ ውስጥ ያላቸው ሚና
    በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ውስጥ የኢትዮጵያ የስነ-ጽሁፍ ሁኔታ
    ለጸሀፊዎች የመሰረተ-ልማት እና ድጋፍ ያለበት ሁኔታ
    ንባብን እንዲሁም መጻፍን ለማበረታታት መደረግ ስላለባቸው የማበረታቻ ስራዎች
    ትምህርት፣ጥልቅ ስሜት እና ተሰጥኦ ያላቸው ግንኙነት
    ባህልን በመጽሐፍት አማካይነት ለትውልድ ማስተላለፍ እንዲሁም ፖሊሲ እና ህትመት ያለበት ሁኔታ

    ይመልከቱ፣ያጋሩ እንዲሁም የውይይቱ አካል ይሁኑ!

    ተጨማሪ የባህል፣ፈጠራ እና ማኅበረሰብ ላይ የተዘጋጁ የፖድካስት ይዘቶች እንዲደርስዎ ላይክ፣ኮሜንት እና ሰብስክራይብ ያድርጉ፡፡


    Writing Our Truths: The State of Literature in Ethiopia

    Episode 7 – CfCA Ethiopia Podcast

    Featuring: Writer Yezina Worku with Teshome Wondimu

    In this powerful episode, we sit down with renowned Ethiopian writer Yezina Worku to explore the challenges and opportunities in the world of Ethiopian literature today.

    From cultivating a reading culture to the role of policy, publishing struggles, language diversity, and the future of storytelling in Ethiopia — this conversation dives deep into what it means to write our truths and build a literary future.

    Topics include:

    The writer’s role in society
    The state of literature in different Ethiopian languages
    The lack of infrastructure and support for writers
    Efforts that need to be carried out to promote reading and writing
    The intersection of education, passion, and talent
    preservation of culture through books, the status of publishing and policy

    Watch, share, and be part of the conversation.

    Don’t forget to like, comment, and subscribe for more content on culture, creativity, and community.

    #1percentforculture #sustainablepublicfunding

    Show More Show Less
    1 hr and 7 mins
  • Sounds of a Nation: The Ethiopian Music Scene - CfCA - Ethiopia #6
    Aug 8 2025

    ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት | ክፍል 6

    ርዕስ፡ የሀገር ድምፅ-የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወግ

    እንግዳ፡ ጆርጋ መስፍን - ሳክስፎኒስት፣ሙዚቃ አቀናባሪ

    አዘጋጅ፡ ተሾመ ወንድሙ - የሰላም እና ሙዚቃዊ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ

    በዚህ የኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት ክፍል የኢትዮጵያን ሙዚቃ ትሩፋት፣የአሁን ተግዳሮቶቹን እንዲሁም ለወደፊት ያለውን ከፍተኛ አቅም እንዳስሳለን፡፡

    እንግዳችን ጆርጋ መስፍን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ትሩፋት ላይ በማተኮር ከቅዱስ ያሬድ እስከ ዛሬ ዘመን የሚገኘው ወጣት መር ፈጠራን ይዳስሳል፡፡ ጆርጋ መስፍንና ተሾመ ወንድሙ በጋራ በመሆን እንደ የኦሪጅናል ካሴቶች አለመኖር፣ተገቢ የክምችት ሁኔታ አለመኖር፣ጊዜ ያለፈባቸው ወይም ተደራሽ ያልሆኑ ኮንትራቶች እና ስለባህላዊ መሰረተ ልማት አስፈላጊነት ይዳስሳሉ፡፡

    የሚዳሰሱ ርዕሶች ዝርዝር

    · ሙዚቃን ጠብቆ የማቆየት ተግዳሮቶች እና የብሔራዊ ክምትቶች መጥፋት
    · በሙዚቃ ኮንትራቶች እና በቅጂ መብት ጥበቃ የሚያስፈልጉ የህግ መሻሻሎች
    · በወጣቶች የሚመራ ህዳሴ እና እንደ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ያሉ ተቋማት ጠቃሚነት
    · በአገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ቱር ማድረግ
    · የኢትዮጵያ ሙዚቃ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስኬታማ እንዲሆን ለምን ወጥነቱን መጠበቅ እንዳለበት
    · የባህል ዘርፉን የሚገነቡ እንጂ የማያፍኑ ፖሊሲዎችን መገንባት

    ይህ ክፍል ፖሊሲ አውጪዎች፣አርቲስቶች፣አስተማሪዎች እና የባህል መሪዎች የኢትዮጵያን ልዩ የሙዚቃ ድምጸት ጠብቀው እንዲያቆዩ እና እንዲለውጡ ጥሪ የሚያቀርብ ነው፡፡


    🎙️ Connect for Culture Africa – Ethiopia Podcast | Episode 6
    Title: “Sounds of a Nation: The Ethiopian Music Scene”
    👤 Guest: Jorga Mesfin – Saxophonist, Composer
    🎤 Host: Teshome Wondimu – Founder & Executive Director, Selam

    In this powerful episode of Connect for Culture Africa – Ethiopia Podcast, we explore the state of Ethiopian music—its legacy, its current struggles, and its immense future potential.

    Our guest, Jorga Mesfin, reflects on the rich musical heritage of Ethiopia, from the time of Saint Yared to today's youth-led innovation. Together with host Teshome Wondimu, they unpack urgent issues: the loss of original cassettes, the lack of proper archiving, outdated or inaccessible music contracts, and the need for strong cultural infrastructure.

    🎶 Topics discussed include:

    The crisis of music preservation and the loss of national archives
    Legal reforms needed in music contracts and copyright protection
    Youth-driven revival and the importance of institutions like Yared Music School
    Touring locally vs. internationally
    Why Ethiopian music should maintain its authenticity for global success
    Building policies that support—not stifle—the cultural sector
    This episode is a call to action for policymakers, artists, educators, and cultural leaders to unite in preserving and evolving Ethiopia’s sonic identity.

    Show More Show Less
    1 hr and 27 mins
  • The Reel Story: A Conversation on Ethiopia’s Film - CfCA Ethiopia #5
    Jul 18 2025

    በኢትዮጵያ ፊልም ዙሪያ ያተኮረ ውይይት| ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት - ምእራፍ 2

    ወደ ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ (ሲኤፍሲኤ) ኢትዮጵያ ፖድካስት እንኳን በደህና መጡ፤ በዚህ ክፍል በባህል እና በዘላቂ ልማት መካከል ያለውን ቁልፍ ግንኙነት እንዳስሳለን፡፡

    በዚህ በኢትዮጵያ ፊልም ዙሪያ ያተኮረ ውይይት ላይ ከዝነኛው ፊልም አዘጋጅ ሄኖክ አየለ እንዲሁም ተሾመ ወንድሙ ጋር የኢትዮጵያ ፊልም ዘርፍ ላይ ወቅታዊ እና ግልጽ ውይይት እናደርጋለን፡፡

    በዚህ ክፍል የሚከተሉትን ቁልፍ ጥያቄዎችን እናነሳለን፡

    • የኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስትሪ እንደ ኔትፍሊክስ ላሉ ዓለም አቀፍ መተግበሪያዎች ዝግጁ ነው?

    • የፊልም ትምህርትን፣የገንዘብ ድጋፍን እና የፖሊሲ ትግበራን ወደ ኋላ እየጎተተው የሚገኘው ምንድነው?

    • በፍጥነት እየተቀያየረ በሚገኝ ዲጂታል ዓለም ላይ የቅጂ መብት እንዴት ሊከበር ይችላል?

    • በባህል ልማት ውስጥ መንግስት እና ኢንቬስተሮች ምን አይነት ሚና መጫወት አለባቸው?

    ከሲኒማ አዳራሾች የመጥፋት ሁኔታ አንስቶ እስከ በወጣቶች ስለሚመራ ፈጠራ እና የአገር ውስጥ የስርጭት አማራጮች በመዳሰስ- በዚህ ክፍል የኢትዮጵያ ፊልም ዘርፍ የት ጋር እንዳለ እና ቀጥሎም ወደ የት መሄድ እንዳለበት እንመለከታለን፡፡

    በአፍሪካ ባህል ላይ የተሻለ ኢንቨስትመንት እንዲኖር የምንጠይቅበትን ይህን ክፍል ይመልከቱ፣ያጋሩ እንዲሁም ቻናሉን ሰብስክራይብ ያድርጉ፡፡ ይህ ክፍል በስፖቲፋይ እና አፕል ፖድካስት ላይም ይገኛል፡፡

    Connect with us: https://cfcafrica.org https://www.facebook.com/CFCA23 https://www.instagram.com/cfcafrica https://www.linkedin.com/company/connectforcultureafrica/posts/?feedView=all https://x.com/cfcaafrica

    Show More Show Less
    1 hr and 15 mins
No reviews yet
In the spirit of reconciliation, Audible acknowledges the Traditional Custodians of country throughout Australia and their connections to land, sea and community. We pay our respect to their elders past and present and extend that respect to all Aboriginal and Torres Strait Islander peoples today.