• የዓለም ዜና፤ ታሕሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ
    Dec 16 2025
    አርስተ ዜና፤ --ኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮችና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ረቡዕ በሚያካሂደዉ የጋራ ስብሰባ የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ንግግር እንደሚያደርጉ ታወቀ። ሞዲ መዲና አዲስ አበባ ገብተዋል።--ሱዳን በድጋሚ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ቀዉስ መዘርዝር ቀዳሚ የዓለም ሃገር መሆንዋ ተገለፀ። ከሱዳን ቀጥሎ የፍልስጤም ግዛቶች ፤ኢትጵያና ሄይቲ በዓለም አቀፉ የሰብዓዊ ቀዉስ መዘርዝር 3ኛ ደረጃ ላይ በየተራ ተቀምጠዋል።--በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ያለውን ጦርነት ለማስቆም እየተካሄደ ያለዉ ዉይይት እና ድርድር ፤ ለሰላም «ከምንጊዜውም በላይ ቅርብ ሆንዋል» ሲሉ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ።
    Show More Show Less
    10 mins
  • የታሕሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    Dec 15 2025
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዳሰነች ወረዳ መስተዳድር ለሁለተኛ ጊዜ የሕዝብ እንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን አስታወቀ ፡፡ኤርትራ ያለፍርድ ያሰረቻቸውን ወደ 10,000 የሚገመቱ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንድትፈታ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ። ሳውዲ አረቢያ በመገባደድ ላይ ባለው ጎርጎሮሳዊ 2025 ዓመተ ምህረት የሞት ቅጣት በመፈጸም የዓለም ክብረወሰን መያዝዋን ዘገባዎች አመላከቱ።
    Show More Show Less
    11 mins
  • የታሕሳስ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    Dec 14 2025
    በሱዳን በምትገን የዲሊንጅ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 7 ስቪሎች መገደላቸውን የሆስፒታል ምንጮች አስታወቁ። የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ «በኢራን ይደገፋል» ያለው የሒዝቦላህ አባላት ናቸው ያላቸውን 3 ታጣቂዎች መግደሉን አስታወቀ። በአውስትራልያ ቦንዲ በተበለ የባሕር ዳርቻ 2 ጠመንጃ የታጠቁ ግለሰቦች ዘመናት ያስቆጠረውን ባሕላዊ ክብረበ ዓላቸውን ሲያከብሩ በነበሩ ይሁዲዎች ላይ ዛሬ በፈጸሙት የተኩስ እሩምታ ቢያንስ 12 ሰዎች መሞታቸውን ተሰማ።
    Show More Show Less
    9 mins
  • DW Amharic የታኅሳስ 04 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    Dec 13 2025
    የኢትዮጵያ እና የኤርትራ “ሉዓላዊነት፣ ነጻነት እና የግዛት አንድነት እንዲከበር” ብሪታኒያ እና ቱርክን ጨምሮ አምስት ሀገራት በጋራ ጥሪ አቀረቡ። ሁለቱ ሀገራት “ማንኛውንም ውጥረት ወይም አለመግባባት በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈቱ” የአውሮፓ ኅብረት ጠይቋል። ኤርትራ ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ድርጅት አባልነት ራሷን ለማግለል ያሳለፈችው ውሳኔ እንዳሳዘናት ጅቡቲ አስታወቀች። ርዋንዳ በምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የወሰደችው እርምጃ በዶናልድ ትራምፕ አሸማጋይነት በዋሽንግተን የተፈረመውን የሰላም ሥምምነት እንደሚጥስ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ አስታወቁ።
    Show More Show Less
    9 mins
  • የዓለም ዜና ታህሳስ 3 ቀን 2028 አርብ
    Dec 12 2025
    -ዶይቸ ቬለ (DW) ሁለት ዘጋቢዎቹ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን በቋሚነት መታገዳቸውን አጥብቆ ተቃወመ። ሰባቱ ጋዜጠኞች ስራቸዉን ቀጥለዋል። ኢትዮጵያና ኤርትራ አንዳቸው የሌላውን የግዛት አንድነት እንዲያከብሩ የተመድ አሳሰበ። በሁለቱ ሀገራት መካከል“እንደገና የተቀሰቀሰዉ አዲስ ውጥረት” እንዳሳሰበውም ገልጿል። በሌላ በኩል ኤርትራ እራስዋን ከኢጋድ አባልነት አገደች። የትራምፕ አስተዳደር በዩናይትድ ስቴትስ፣ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ህጋዊ መኖርያ ፈቃድን በግዚያዊነት ማገዱን አስታወቀ።ጀርመን በሰሜን ኢትዮጵያን ለሰላም ግንባታ፣ ለማረጋጋት እና ለግጭት መከላከል ጥረቶች የሚውል ተጨማሪ የ5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገች።
    Show More Show Less
    13 mins
  • የታኅሣሥ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    Dec 11 2025
    ጋዜጠኛ እዮብ ሽመልስ በአስቸኳይ እንዲፈታ CPJ ጠየቀ፤ ከ400 በላይ ንፁሀን ዜጎች በምስራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተገደሉ፤ ዩናይትድ ስቴትስ የደቡብ ሱዳንን መንግሥትን አስጠነቀቀች፤ በክሮኤሺያ-ቦስኒያ ድንበር አቅራቢያ ጀልባ ሰምጣ ሶስት ስደተኞች ሞቱ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ነዳጅ የጫነች የቬንዙዌላ መርከብ በቁጥጥሯ ስር አዋለች፤በዩክሩን ሰው አልባ አይሮፕላኖች የሩሲያ አይሮፕላን ማረፊያዎች ስራ ተስተጓጎለ
    Show More Show Less
    11 mins
  • የታኅሣሥ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    Dec 10 2025
    በከባድ የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው የተገኙት የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር የቀድሞ ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሣ የ13 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው። በዓለም የሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር የሚውለው የገንዘብ ድጋፍ እየቀነሰ፤ ፀረ መብት ለሆኑ እንቅስቃሴዎች የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ እየጨመረ መሆኑን የተመድ አመለከተ። ሩዋንዳ ዴሞክራቲክ ኮንጎ እና ቡሩንዲ ሆን ብለው የሰላም ስምምነቱን እየጣሱ ነው ስትል ከሰሰች። ዴሞክራቲክ ኮንጎ በበኩላ ዩናይትድ ስቴትስ ሩዋንዳን አደብ ታስገዛልኝ ብላለች። ሩሲያ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከምዕራብ ሃገራት መሪዎች ብቸኛው የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ የሚገዳቸው መሪ ናቸው አለች።
    Show More Show Less
    11 mins
  • የማክሰኞ ኅዳር 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    19 mins