የዓለም ዜና cover art

የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

By: DW
Listen for free

About this listen

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።2025 DW Politics & Government
Episodes
  • የታሕሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    Dec 15 2025
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዳሰነች ወረዳ መስተዳድር ለሁለተኛ ጊዜ የሕዝብ እንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን አስታወቀ ፡፡ኤርትራ ያለፍርድ ያሰረቻቸውን ወደ 10,000 የሚገመቱ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንድትፈታ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ። ሳውዲ አረቢያ በመገባደድ ላይ ባለው ጎርጎሮሳዊ 2025 ዓመተ ምህረት የሞት ቅጣት በመፈጸም የዓለም ክብረወሰን መያዝዋን ዘገባዎች አመላከቱ።
    Show More Show Less
    11 mins
  • የታሕሳስ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    Dec 14 2025
    በሱዳን በምትገን የዲሊንጅ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 7 ስቪሎች መገደላቸውን የሆስፒታል ምንጮች አስታወቁ። የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ «በኢራን ይደገፋል» ያለው የሒዝቦላህ አባላት ናቸው ያላቸውን 3 ታጣቂዎች መግደሉን አስታወቀ። በአውስትራልያ ቦንዲ በተበለ የባሕር ዳርቻ 2 ጠመንጃ የታጠቁ ግለሰቦች ዘመናት ያስቆጠረውን ባሕላዊ ክብረበ ዓላቸውን ሲያከብሩ በነበሩ ይሁዲዎች ላይ ዛሬ በፈጸሙት የተኩስ እሩምታ ቢያንስ 12 ሰዎች መሞታቸውን ተሰማ።
    Show More Show Less
    9 mins
  • DW Amharic የታኅሳስ 04 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    Dec 13 2025
    የኢትዮጵያ እና የኤርትራ “ሉዓላዊነት፣ ነጻነት እና የግዛት አንድነት እንዲከበር” ብሪታኒያ እና ቱርክን ጨምሮ አምስት ሀገራት በጋራ ጥሪ አቀረቡ። ሁለቱ ሀገራት “ማንኛውንም ውጥረት ወይም አለመግባባት በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈቱ” የአውሮፓ ኅብረት ጠይቋል። ኤርትራ ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ድርጅት አባልነት ራሷን ለማግለል ያሳለፈችው ውሳኔ እንዳሳዘናት ጅቡቲ አስታወቀች። ርዋንዳ በምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የወሰደችው እርምጃ በዶናልድ ትራምፕ አሸማጋይነት በዋሽንግተን የተፈረመውን የሰላም ሥምምነት እንደሚጥስ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ አስታወቁ።
    Show More Show Less
    9 mins
No reviews yet
In the spirit of reconciliation, Audible acknowledges the Traditional Custodians of country throughout Australia and their connections to land, sea and community. We pay our respect to their elders past and present and extend that respect to all Aboriginal and Torres Strait Islander peoples today.